Showing posts with label ዜና ደብረ ምሕረት. Show all posts
Showing posts with label ዜና ደብረ ምሕረት. Show all posts

Tuesday, February 23, 2016

የካቲት12 በኢጣሊያ በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውን በማሰብ ዝክረ ሰማዕታት መንፈሳዊ ጉባዔ ተከናወነ፡፡



የካቲት13/2008/ የደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት /ቤት ‹‹ዝክረ ሰማዕታት›› በሚል ርዕስ ልዩ መንፈሳዊ አከናወነ።በጉባዔው የሰማዕትነት ህይወት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዓውደ ጥናት የቀረበ ሲሆን በቀረበው ዓውደ ጥናት መሰረት

አሁን ያለን ክርስቲያኖች የሰማዕትነት ህይወት ታላቅ ዋጋ ያለው መሆኑን በመገንዘብ፣ያለፉ አባቶቻችን ሰማዕታትን ህይወት ማወቅ፣ለቀጣዩ ትውልድ ማሳወቅ በትንሹ ቢሆን በያለንበት ቦታ ለሃይማኖታችን መክፍል ያለብንን ዋጋ  መከፍል እንዳለብን በውይይቱ በስፋት የተነሳ ሲሆን ይልቁንም ጣሊያን የካቲት12/1929ዓ/ም   በኢትዮጵያንና ፣በአብያተ ክርስያናት ላይ የፈፀመው አረመኔያዊ ድርጊት አባቶቻችን ያለፍርሃት ታግሰው ሰማዕትነትን መቀባለቸው ዛሬ ቤተ ክርስቲያን እና ሀገራችን ማንነቷ ተጠበቆ ከትውልድ ትውልድ እንዲዘልቅ ያደረገ ታላቅ ተግባር እንደሆነ በስፋት የተገለጸ ሲሆን በተለይም እንደ አቡነ ጴጥሮስ ያለ አባት ለሀገርም ለቅዱስት ቤተ ክርስቲያን ማንነት መጠበቅ ትልቅ ድርሻ ያላቸው ሲሆን ተተኪው ትውልድም ‹‹ውጭ ናፋቂ፣የአውሮፓውያን የሉላዊነት ተገዥ››ከመሆን ይልቅ የሀገሩን ታሪክና የአባቶቹን መስዋዕትነት ከልቡ ገንዘብ ማድረግ እንዳለበት በስፋት ተነስቷል፡፡ከዚህ ባሻገር መነባንብ፣ስነ ግጥም፣መዝሙር የመርሐ ግብሩ አካሎች ነበሩ፡፡

Wednesday, November 4, 2015

መጋቤ ካህናት አባ ብርሃኑ እንየው በህይወተ ሥጋ አረፉ

መጋቤ ካህናት አባ ብርሃኑ እንየው በህይወተ ሥጋ ጥቅምት21/2008ዓ/ም አረፉ፡፡ ስርዓተ ቀብሩም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮችና በርካታ ምዕመን በተገነኙበት ጥቅምት22/2008ዓ/ም ተፈመሟል፡፡ሰለ አገልግሎታቸውና ስለ ሰሯቸው ስራዎች አከታትለን እናቀርባለን፡፡

Tuesday, May 26, 2015

የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያ ‹‹ዝክረ ያሬድ›› ጉባዔ ተከናወነ፡፡




የደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት ግንቦት16/2007ዓ/ም  ‹‹ዝክረ ያሬድ›› በሚል ርዕስ የቅዱስ ያሬድን ታሪክ፣ስራዎችና ለቤተ-ክርስቲያን ያበረከተውን አስተዋጽኦ ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲንን በመገበዝ ሰፊ በሆነ መንገድ በሰንበት ት/ቤቱ አደራሽ አከበረ ፡፡በጉባዔው ከ200 በላይ አባላት የተሳተፉ ሲሆን ያሬዳዊ ዝማሬ፣ቅኔ  ጭውወትና ከሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን ጋር የተደገረ የአብርሐም ቤት እንግዳም የመርሐ-ግብሩ አካላት ነበሩ፡፡በጉባዔውም የቅዱስ  ያሬድን  ስራዎች ከማንሳት በስተጀርባ አሁን  ያለው ትውልድ  አብነት ትምህርትን ትከረት በመስጠት መማር እንዳለበት በስፋት በመምህራኑና በተፋታፊዎች ተገልል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰንበት ት/ቤቱ የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያ ጉባዔ ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ መካሄዱን የሰንበት ት/ቤቱ መርሐ-ግብር ክፍል አያይዞ ገልጿል፡፡

Thursday, July 3, 2014

ቅዳሴ ቤቱ ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል



  
ሰኔ26/2006ዓ/ም
   ‹‹ኔቅላን ››በሚባል አገር  በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ስም የተሰራ ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ስራው ተፈጽሞ ሥርዓተ ቅዳሴ ሰኔ 26 ቤተ ክርስቲያን በሚከናወንበት ጊዜ ከቀድሞ ቅዱስ ገብርኤል የበለጠ ተአምራት አደረገ፡፡



በዚች ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ በሚከናወንበት መዛነቢያ/የበር ጉበን/ ላይ እንደ ላብ ጠብታ ጠብ የሚል ውሀ አለ፤ባገሩም ሁሉ ላይ ረሃብ ይሆን ነበር፡፡ዳግመኛም እንደዝናም አወራረድ በኃይል የሚወርድበት ጊዜ አለ፡፡ይህ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ በሀገሩ ላይ ጥጋብ ይሆናል፡፡ስለዚህም የሀገሩ ሰዎች በእነዚህ በሁለቱ የውሀ ምልክት የረሀቡንና የጥጋቡን ዘመን ለይተው ያውቁ ነበር፡፡ይህም ምልክት በዚያው በተወሰነው ቀን በየዓመቱ ሲደረግ ኖረ::

የሞቱ የአባቶቻችንና የእናቶቻችን ነፍስ በመንግስተ ሰማያት ያሳርፍ ዘንድ እንዲሁም በዚህ ዓለም በሚመጣው ዓለም ጭንቀታችንን ያቃልልልን ዘንድ ዳግመኛም ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ ክብርን እንዲያድለን ይህችን ቀን ከፍ ከፍ እናድርጋት፡፡-----------//--------------
‹‹ የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነቱና ጥበቃው አይለየን››

ደ/ም/አ/ቤ/ቅ/ገ/ሰ/ት/ቤት ጎንደር