Thursday, November 6, 2014

ወርኃ ጽጌ (ክፍል ሁለት)



ወርኃ ጽጌ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 6 ያለው 40 ቀን ድረስ ያለው ጊዜ ጽጌ ይባላል ፡፡ ጽጌ የሚለው ቃል /ጸገየ/ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም አበባ ማለት ነው ፡፡ ይህም ወቅት በተለየ ኢየሩ ሕይወት ለአላቸው ፍጥረታት ሁሉ ተስማሚና አመቺ ነው ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከልጇ ጋር ያደረገችውን ስደት የሚታወስበት ወቅት በመሆኑም ጾመ ጽጌ የማይምርት----ነዉ፡፡በአበባ  ወራት ከመታሰቡ ጋር ተያይዞ ስያሜዉን አግኝቷል፡፡ምግበ ስጋ  ምግበ ነዊሰ ---መድኃነታችንን አስገኝታለች ጽጌ /አግባ/ የእመቤታችን የንጽህናዋ ፣የቅድስናዋ ምሳሌ ነው፡፡በሌላ በኩልም ጌታችን ጽጌ /አበባ ይባላል ፡፡
በወ ጽጌ ሰማይ ለክዋክብት አሸብርቃ የሚታይበት ፣ ወንዞችና ጀረቶች የጠራ ውሃ የሚያፈሱት ንጹን አየር የሚነፍስበት  ፤አዕዋፍ ከተሰደዱበት እተመለሱ የሚዘምሩበት ፣ እንሰሳትም በክረምትወራት የለመለመዉን ሳር እየጋጡ የጠራወን ውሃ እየጠጡ የሚፈነጥዙበት ጊዜ ነው ፡፡በዚህ ወቅት ምንም  እንኳን ምድር በልምላሜ የምታጌጥ ቢሆንም  ወቅቱ ካለፈ በኋላ አበቦቿ ጠውልገው ቅጠሎቿ ይረግፋሉ ፡፡ ሥጋ ለባሸ ሁሉ ሣር ነው ክብረም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው ፡፡ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች ፡፡ ኢሳ 40$6-20 እንዳለ የሥጋ ዘመን አልፉ ወደ ---- ነፍስ የመሻጋገራችንን ጉዳይ ሥጋን እንድናስብ ያለምንም ከቱነት በሃጋድ የሚያሳየን ጊዜ ነው ፡፡ በዚህም ምክንያት በተዘክውተ ሞት ትንሣኤ ህሊና አግኝተን በንስሐ እንድንመላለስ ያስተምረናል ፡፡
ጾም ጸጌ በቀናና ቤተ-ክርስቲያን የተደመገገ ባሆንም መንፈሳዊያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፍቃድ የሚጾሞት ጾም የትሩፋት ጾም ነው ፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ስራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፉ ይናገራል ፡፡ ሉቃ 7$47 የሚጾምበት ምክንያት ሄሮድስ ህፃናትን በቅናት ተነስቶ በሰፈነው ጊዜ እመቤታችን ከልጃ ጋር ያደረገችውን የመድረ ግብፅን ስደት በማሰብ ነው ፡፡
ስደት ማለት መበታትን ፣ መለያየት ፣ መባረር ፣ መከልከል ፣ መጥፋት ፣ መታጣት ፣ ቦታን መልቀቅ ፣ ከሃገር ከዘመድ መራቅ ፣ መፍለስ ፣ መነቀል ማለት ነው ፡፡ ስደት በተሰራው በደል ፣ በተፈጥሮአዊ ችግሮች ስለ ጽድቅ ሊመጣ ይችላል ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን አህዛብን ሆሎ በብረት ዘንግ የሚገዛቸውን ወንድ ልጅ በመውለዷ ለጌታችን ለመዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ስደት መከራ ተቀበለች ፡፡
ንጉስ ሂሮድስ የጌታቸወን መወለድ ከሰብዓ--- ሳገል ስሞት የመንግስቱን ተቀናቃኝ የተነሳበት ስለ መላው ይከተለው ዘንድ ሲያስብ ማዕምረ ኃቡአት እግዚአብሔር መላኩን ወደ ቅዱስ ዮሲፍ ላከ ፡፡ መላኩም በህልም ለዮሴፍ ታይቶ / ሔሮድስ / ህፃኖን ሊገለው ይፈልጋል  እና ተነሳ ህፃኑም እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሸሽ እስከነንግረህም በዚያ ተቀመጠ ፡፡ ማቴ 2$13 እንሱም በነቢዩ የሳያስ እንሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብፅ ይመለሳል ፡፡ ኤሳ 19$1 የተባለው ይፈፅም ዘንድ እመቤታችንና ጌታችንን ይዞ ተሰዷል .3 ዓመት ከ6 ወርም በግብጽ በረሃ እስከ ኢትዮጵያ ተከራተዋል ፡፡ በሰቆቃው ድንግል ድረስ /ፀሐይን የምትለብስ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ዘንድ ከሔድሮስ ልጅሽን በሸሸች ጊዜ የደረሶባትን ችግሮች ፣ መረቃን የሚጠሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሽዋ ግለት እንደ----- ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋይም ባላለቀሰ ነበር ፡፡ በማለት ስደቱን ገልፃል ፡፡
ይኼንንም የደረሰባትን መከራና ስደት በማሰብ ሞአመናን የፅጌ ፆም በፈቃዳቸው ይፆሙታል ፡፡
መሰደድ ነበር ነው ካጥንት ከጣዋቱ፣
መከራም እንደዚው በየአግባብነቱ፡፡
ያገኘው እያጣ ያጣው እያገኝ፣
አዋቂው ተረስቶ ሞኙም እያሞኘ ዘመኑተናኘ፡፡
በዳያቢሎስ እወቀት አዳም መሞኘቱ ፣
በሰው አሰተሳሰብ ምን ይሆን ምክንያቱ ፡፡
ገነታዊ ፍጡር ቦታ መለውጡ ፣
የብብቱን ጥሎ ማየት ወደ ቆጡ ፡፡
ይህም ባለገረመ አጥፊ መሰደዱ ፣
እንዲሁ ነውና የፍጡር ልማዱ ፡፡
እኔን የገረመኝ የፈጣሪው ስራ፣
ሰደትን በስደት ቅድሱ ሲጠራ ፡፡
የፈጣሪ ስራ ምንግዚም ግሩም ነው ፣
ሰደትን በስደት ቀድሶ አከበረው ፡፡


ብሒለ አበው
Ø <<ድንግሊቱ ሔዋን የእባብንም ቃል ሰምታ አለመታዘዝንና ሞትን ፀነሰች $ ወንድሞን የሚገድልውን የሞትን ልጅ ገዳይ ቃየልን ወለደጀች፡፡ ድንግል ማሪያም ግን የብርሃናዊው መልአክ የቅዱስ ገብርኤል ብስራት ሰምታ ታዛዥ ሆነች (እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች) ህይወት ክርስቶስን ፀነሰች ለህዝብውም የሚሞተውን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወለደች  >>
ቅዱስ ዮስጢኖስ
Ø << አንድት ክፉ ቃል መልካሙ ሰው እንኳን ክፉ ታደርገዋለች$አንድት መልካም ቃል ግን ክፉውን ሰው መልካም ታደርገዋለች  >>
                                                                                አባ መቃርዮስ
Ø <<ፀሎት የነብስን ተራ ስሜቶች ፀጥ ያረጋል $ የቁጣን አመፅ ያብርዳል $ ቅናትን ያጠፋል $ ክፉ ፍላጉቱችን ይበትናል $ የአለማዊ ነገሮች ፍቅር ያመነምናል $ ለነፍስም ታላቅ ሰላምና እርቅን ያመጣል፡፡ >>
                                                                        ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

No comments:

Post a Comment

ደ/ም/አ/ቤ/ቅ/ገ/ሰ/ት/ቤት ጎንደር