Wednesday, March 16, 2016

ሰማዕትነት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ/ክፍል አንድ/

ሰማዕት‹‹ ሰምዐ ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም መመስከር ፣ምስክር መሆን፣ያየውን የሰማውን ተናገረ ወይም አየሁ ሰማሁ ማለት ነው፡፡‹‹ስምዕ››ለአንድ ሲሆን ‹‹ሰማዕት›› ለብዙ ቁጥር ነው፡፡‹‹ሰማዒ›› የሚሰማ የሚቀበል ሰሚ መስካሪ ‹‹ሰማዕት›› ማለትም ምስክሮች፣ሃይማኖታቸውን መስክረው በሰማዕትነት የሚሞቱ ማለት ነው፡፡
  • ክርስቶስ ‹‹ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝን ሁሉ እኔ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እምሰክርለታለሁ፡፡በሰዉ ፊት የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባተ ፊት እክደዋለሁ፡፡››
  • ስለሃይማኖት ፣ስለ ቤተ ክርስቲያን ሲሉ በአደባባይ ቆመው መስክረው ሰማዕትነትን የተቀበሉ በርካቶች ናቸው፡፡ እንዚህም በየዘመኑ የተነሱ ዓላውያን ነገስታት‹‹ፈጣሪን ካዱ፣ለጣዖት ስገዱ ሲሏቸው፣‹‹ ፈጣሪያችንን አንክድም ፣ለጣዖት አንሰግድም የኑፋቄ ትምህርትንም አንቀበልም›› ብለው ሳያፍሩና ሳይፈሩ በአደባባይ መስክረው ጸዋትወ መከራ በመቀበል ለክብር አክሉል በቅተዋል፡፡ 
  • ሰማዕት፤- ስለ እግዚአብሔርና፣ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲን ክብር በአጣቃላይ ስለ ሃይማታቸው በእውነት በመመስከራቸው ጀርባቸውን ለግርፋት፣ሰውነታቸውን ለእሳት ፣እግራቸውን ለሰንሰለት፣አንገታውን ለስለት ስለሰጡ፣በድንጊያ ተወግረው፣በመንኩራኩር ተፈጭተው፣በጦር ተወግተው፣አልያም በግዞትና በስድት ፣በዱር በገደል ተንከራተው ለዐረፉ ሁሉ ቅዱሳን አባቶታችንና ቅዱሳት እናቶችቻን የሚሰጥ እና ተጋድሏቸውን ጠቅለል አድርጎ የሚገልጽ ቃል ነው፡፡
     
  • ቅዱስ ኤፍሬም ‹‹ ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፣ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር መንግስት አፈሰሱ፣ስለመንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ፡፡››ውዳሴ ማርያም
     
  • ዘመና ሰማዕታት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የስደት ዘመን በመባል ይታወቃል፡፡‹‹ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፡፡››ማቴ5፤10 ጌታችንም ወደ ግብጽ ተሰዶ ስደትን ለሰማዕታት ባርኮላቸዋል፡፡
                              የሰማዕታት ዓይነቶች


.ሰማእትነት ዘእንበለ ደም 
በስለት መሰየፍ፣በእሳት መቃጠል ሳይሆን በስደት፣በእስራት፣ግዞት፣ስድብ ነቀፌታ ሲደርስባቸው በአኮቴት ና በትዕግስተ የሚቀበሉ ናቸው፡፡ዓለምን ያለማንኛውም ሀብትና ንብረት ንቀው የተዉ፣በጾም፣በጸሎት፣በስግደት፣በትህርምትና በንስሐ ህይወት የሚደረግ ተጋድሎ ነው፡፡ከአጋንንት ጋር እየታገሉ የሚኖሩ ናቸው፡፡ምሳሌ፤- ገዳማውያን ሰማዕታትና መናንያን ሰማዕታት ናቸው፡፡
፪. ደመ ሰማዕት
ደማቸውን ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ክብር፣ስለ ቤተ ክርስቲያን፣ሲሉ ያፈሰሱ ናቸው፡፡ይህም የሰማዕትነት የመጨረሻ ደረጃ መገለጫ ነው፡፡ሰው

ም ወደ ዚህ ደረጃ ሲደርስ የሚችለው ውስጣዊ ፍትዎቱን ታግሎ ሲያሸንፍ አፍአዊ ንብረቱን ንቆ ሲተው በፈቃደ ሥጋው ላይ ነፍሱን ሲያሰለጠን በአጠቃላይ ራሱን መግዘት ሲችል ነው፡፡ምሳሌ፤-ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ቅዱስ እስጢፋኖስ፣አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊ ወ.ዘ.ተ
                                   ዓለማቀፍ ሰማዕታት
‪#‎በዘመነ‬ ብሉይ/ከክርስቶስ ልደት በፊት
*አቤል የሰማዕታት መጀመሪያ ነው፡፡ዘፍ4፤2
*ናቡቴ፣ኢሳይያስ፣ኤርሚያስ፣የአንጢያኮስ ዘመን ካህኑ አልአዛር፣ሕዝቅኤል፣ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ወ.ዘ.ተ
በዘመነ ሐዲስ/ከክርስቶስ ልደት ወዲህ/
*ዘመኑ ዓመተ ምህረት ዓመተ ሥጋዌ፣ዘመነ ሐዲስ ይባላል፡፡
*በዚህ ዘመን በርካታ ክርስቲያኖች በየዘመኑ አላውያን ነገስታት ብዙ መካራ ደርሶባቸዋል፡፡ኦርቶዳክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብሔረ ሙሉዳቸውን፣ጥንተ ነገዳቸውን ፣የገድላቸውን ጽናትና የስነ ጽሁፋቸውን ብስለት መዝግባ አስቀምጣለች፡፡
ህጻናተ ቤተ ልሔም፣ዘካርያስ ወልደ በራክዩ፣መጥመቀ መለኮት ወልደ ዘካርያስ፣ቅዱስ ጴጥሮስ፣ቅዱስ ጳውሎስ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ፣ቅዱስ ፋሲለደስ፣ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወ.ዘ.ተ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ለአብነት ያህል እንጅ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ እስከ 4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እስከ ታላቁ ቁስጠንጢኖስ ዘመነ መንግስት ድረስ አያሌ ክርስቲያኖች በሰማዕትነት ሞተዋል፡፡
  • በዲዮቅሊጢያኖስ ዘመነ መንግስት በግብፅ ብቻ 800,000/ስምንት መቶ ሽ / ክርስቲያኖች በሰማዕትነት ሙተዋል፡፡ከዚህም የተነሳ የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ዘመን የምትቆጥረው በዓመተ ሰማዕታት ነው፡፡
                                 ሰማዕታተ ናግራን/ደቡብ አረብ/የአሁኗ የመን/
ክርስትናን የመሰረተው ፋሚውም የሚባል የሶርያ ተወላጅ ነበር፡፡በየጊዜውም ከቁስጥንጥንያ ብዙ ቀሳውስት ፣ኤጵስ ቆጶሳት እየሄዱ ክርስትናን አሰፉ፡፡በጣም የሚታወቀውም ሐዋርያ አባ ጳውሎስ የሚባል ነበር፡፡ምንም እንኳን መምህሮቻቸው ከቁስጥንጥንያና ሶርያ ቢመጡ የናግራን ክርስቲያኖች/ደቡብ ዓረብ/ እንደጠባቂ የሚያዩት የአክሱምን መንግስት ነበር፡፡ የሀገረ ናግራን ክርስቲያኖች አባታቸው ቅዱስ ኂሩት ይባል ነበር፡፡ አይሁዳዊ ንጉስ/ፊንሐስ/ማዝሩቅ/..በ5ኛው መቶ ክ/ዘ የናግራን ክርስቲያኖች መከራ አጽንቶባቸዋል፡፡ቁጥር የሌላቸው ክርስቲያኖችም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ አባ ጢሞቲዎስና የቆስጥንጥንያ ንጉስ ዮስጢኖስ ለኢትዮጵያዊው ንጉስ አፄ ካሌብ የናግራን ክርስቲያኖችን መከራ በደብዳቤ ላኩለት፡፡ንጉሱም 120,000 በላይ ሰራዊት የንጉስን ሠራዊትና ንጉሱን ድል አደረጉ፡፡/525 ዓ/ም/ ክርስቲያኖችንም አጽናኑ፡፡ይቀጥላል....

No comments:

Post a Comment

ደ/ም/አ/ቤ/ቅ/ገ/ሰ/ት/ቤት ጎንደር