Saturday, June 28, 2014

የመጀመርያው የጎንደር ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዓመታዊ ጉባዔ ተከናወነ

ሰኔ16/2006ዓ/ም የመጀመርያው የጎንደር ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዓመታዊ ጉባዔ ተከናወነ፡፡ ለበርካታ ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የጎንደር ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዓመታዊ ጉባዔ ለመጀመርያ ጊዜ ሰኔ15 /06ዓ/ም በመንበረ መንግስት መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ተከናወነ፡፡በዚህ ጉባዔ በጎንደር የሚገኙ 25 ሰንበት ት/ቤቶች ተካፍለዋል፡፡የጎንደር ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መመስረቻ ጽሁፍና የአንድነቱ የአምስት አመት መሪ እቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡በጉባዔው የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቀለመ ወርቅ አሻግሬ ፤የርዕሰ ከተማው ወረዳ ቤተ ክህነት ሰንበት ት/ቤት ክፍል ኃላፊ መጋቢ ስርዓት ዮሐንስ ባዘዘው፣የደብር አስተዳዳሪዎችና የአብነት መምህራን ተገኝተዋል፡፡

በጉባዔው ማጠናቀቂያ ባለ 9 የአቋም መግለጫ የቀረበ ሲሆን እነዚህም ለሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባዔ መጠናከር ሀገረ ስብከቱ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን፡፡ የሰንበት ት/ቤት አዳራሽ የሌላቸው ሰንበት ት/ቤቶች ተለይተው በሀገረ ስብከቱ ለሰበካ ጉባዔያት መመሪያ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን፡፡ የወጣት ማኅበራት በሰንበት ት/ቤት የቃለ ዓዋዲ ስልጣንና ኃላፊነት ላይ ጣልቃ መግባትና እያደረሱ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖ መፍትሔ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን ፡፡ ባላ መረዳት ሰንበት ት/ቤትን የማያግዙና የማይደግፉ ሰበካ ጉባዔያትና ማህበረ ካህናት በሀገረ ስብከቱ በኩል የግንቤዛ ማስጨበጫ ስራ እንዲሰራና መመሪያ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን፡፡ በየክፍለ ከተማ ለሚደረገው የክፍለ ከተማ የአንድነት ጉባዔ መጠናከር የበኩላችንን ሁሉ ለመወጣት ቃል እንገባን፡፡ የአምስት ዓመቱ መሪ እቅድ የሰበካ ጉባዔ እቅድ እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡ ከዓመታዊ የሀገረ ስብከቱ የበጀት ድልድል ሰንበት ት/ቤት እንዲካተተት እንጠይቃለን፡፡ የአምስት ዓመቱ መሪ እቅድ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ቃል እንገባን፡፡በሚሉ ነጥቦች ላይ የጋራ ስምምነት ከተደረሰ በኋላ በሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪጣጅ ሊቀ አዕላፍ ቀለመ ወርቅ አሻግሬ መመሪያና ትምህርት ተሰጥቷል፡፡በመጨረሻም ጉባዔው በጸሎት ከተዘጋ በኋላ የጉባዔው ፍጻሜ ሁኗል፡፡-------//---------- 

ሰኔ16/2006ዓ/ም የደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት የበጎ አድራጎት ተግባራትን መስራቱን አጠናሮ ቀጥሏል፡፡ 

(1)ከደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት አቢይ ክፍል ከሆኑት መካከል የበጎ አደራጎት ክፍል አንዱ ሲሆን ይህ ክፍል በተለያየ ጊዜ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ሲያከናውን የቆየ ቆይቷል፡፡ክፍሉ በቀበሌ 01 የምትኖር 3 ቤተሰቦች ለምታስተዳደር እናት በሙያዋ ጠላ በመጥመቅ ልጆቿን እንድታስተዳድር በማድረግ ወደ ስራ አስገብቷል፡፡

 (2)በደብረ ምረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንት ት/ቤት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለሚያገለግሉ ረዳት ለሌላው ለአንድ መሪጌታና ለ3 ዲያቆናት የጤና ችግራቸውን በመረዳትና ከፍለው መታከም ባለመቻላቸው ከማዕዶት በጎ አድራጎት ማኅበር ጋር በመነጋገር በነጻ የሚታከሙበትን ሁኔታ አመቻችቷል፡፡ 

 (3)በደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት ስራ የሌላቸው 5 ወንድሞችና 10 ሴቶችን በተለያዩ የእደ ጥበብ ዘርፎች ለአንድ ወር አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡

1 comment:

  1. gena enseralen egziabhier yabertan..............

    ReplyDelete

ደ/ም/አ/ቤ/ቅ/ገ/ሰ/ት/ቤት ጎንደር