Thursday, July 3, 2014

ቅዳሴ ቤቱ ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል



  
ሰኔ26/2006ዓ/ም
   ‹‹ኔቅላን ››በሚባል አገር  በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ስም የተሰራ ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ስራው ተፈጽሞ ሥርዓተ ቅዳሴ ሰኔ 26 ቤተ ክርስቲያን በሚከናወንበት ጊዜ ከቀድሞ ቅዱስ ገብርኤል የበለጠ ተአምራት አደረገ፡፡



በዚች ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ በሚከናወንበት መዛነቢያ/የበር ጉበን/ ላይ እንደ ላብ ጠብታ ጠብ የሚል ውሀ አለ፤ባገሩም ሁሉ ላይ ረሃብ ይሆን ነበር፡፡ዳግመኛም እንደዝናም አወራረድ በኃይል የሚወርድበት ጊዜ አለ፡፡ይህ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ በሀገሩ ላይ ጥጋብ ይሆናል፡፡ስለዚህም የሀገሩ ሰዎች በእነዚህ በሁለቱ የውሀ ምልክት የረሀቡንና የጥጋቡን ዘመን ለይተው ያውቁ ነበር፡፡ይህም ምልክት በዚያው በተወሰነው ቀን በየዓመቱ ሲደረግ ኖረ::

የሞቱ የአባቶቻችንና የእናቶቻችን ነፍስ በመንግስተ ሰማያት ያሳርፍ ዘንድ እንዲሁም በዚህ ዓለም በሚመጣው ዓለም ጭንቀታችንን ያቃልልልን ዘንድ ዳግመኛም ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ ክብርን እንዲያድለን ይህችን ቀን ከፍ ከፍ እናድርጋት፡፡-----------//--------------
‹‹ የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነቱና ጥበቃው አይለየን››

No comments:

Post a Comment

ደ/ም/አ/ቤ/ቅ/ገ/ሰ/ት/ቤት ጎንደር