Wednesday, October 14, 2015

ወርኃ ጽጌ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ወርኃ ጽጌ
ጽጌ የሚለው ቃል ጸገየ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም አበባ ማለት ነው።  በቤተ ክርስቲያን ከመስከረም 26 - ሕዳር 5 ቀን ያሉት አርባ ቀናት “ዘመነ ጽጌ” ይባላል።  በዘመነ ጽጌ ሜዳው፤ ሸንተረሩ በአበባ ያጌጣል።  በክረምቱ ዝናም፤ አረንጓዴ ለብሳ የነበርችው ምድር የተለያዩ ሕብረ ቀለም ባላቸው አበቦች ትሸፈናለች። ጫካው፤ ኮረብታው በአበቦች መዓዛ ይታወዳል። ይህ ወር ጨለማው ክረምት አልፎ ጅረቱ የሚጎድልበት ዘመድ አዝማድ “እንኳን ዘመን ክረምቱን በሰላም አስፈጸማችሁ” እያለ የሚጠያየቅበት ታላቅ የተስፋ መር ነው።


 
  •              በሀገራችን የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ ወራት /ዘመነ ጽጌናቸው፡፡ይህም ወቅት ተራሮች በአበባ የሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡በዚህም ዘመን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ስለ ልብስስ ስለምንትጨነቃላችሁየሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡አይደክሙም፣ አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ ሰሎሞንስ ስንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህእንደ አንዱ አልለበሰም፡፡ እግዚአብሔርን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውንየሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጐደላችሁ እናንተንማ ይልቁንእንዴት እንግዲህ ምን እንበላለን ምንስ እንጠጣለንምንስ እንለብሳለንብላችሁአትጨነቁ ...» /ማቴ.5÷28-33/ በማለት የተናገረውን ቃል በማሰብ መጨነቅ የሚገባንመንግሥተ ሰማያት ለመግባት እንጂ በዚህ ዓለም ስላለው ነገር እንዳልሆነ ተራሮችንበአበባ ያለበሰ አምላክ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረንን እኛን ለኑሮ የሚያስፈልገንንምግብና ልብስ እንደማይነሳን እያሰብን የምንዘክርበት ወቅት ነው፡፡

  •                 እንዲሁም ክቡር ዳዊት «ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ ወሰብእሰ ከመሳዕር መዋዕሊሁ ወከመ ጽጌ ገዳም ከማሁ ይፈሪ፤ አቤቱ እኛ አፈር እንደሆን አስብ ሰውስዘመኑ እንደሣር ነው እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋልና» /መዝ.12÷14-16/ በማለት እንደ ተናገረው የሰው ሕይወት በሣር ይመሰላል፡፡ ሣርአድጐ አብቦ ከዚያ በኋላ ይደርቅና በነፋስ አማካኝነት  የረገፈው ሣር እየተነሣ የነበረበትቦታ ስንኳ እስከማይታወቅ ድረስ ይሆናል፡፡ ሰውም ከአደገ በኋላ በሕማም ፀሐይነትይደርቅና በሞት ነፋስነት ይወሰዳል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ መቃብር ሲወርድ የነበረበት ቦታይዘነጋል፡፡ ስለዚህ ዘመነ ጽጌ ሰው ዘመኑ እንደ አበባ በቶሎ የሚረግፍ መሆኑን በማሰብይህ ዘመን ሳያልፍ መልካም ሥራ ለመሥራት ትንሣኤ ኅሊና የሚነሣበት ጊዜ ነው፡፡ቅዱስ ያሬድ ለዘመነ ጽጌ የሠራው ድጓም ይህንኑ የሰውን ዘመን አጭርነት የሕይወቱንኢምንትነት በዚህ ሕላዌ የተፈጠረ ሰው በዚህ ዓለም ክፉ ሥራ መሥራት እንደሌለበትሁልጊዜ በተዘክሮተ ሞት እንዲኖር የሚያስረዳ ነው፡፡


  •                      በዘመነ ጽጌ ቅዱስ ያሬድ ከደረሰው ድጓ በተጨማሪ ከላይእንደተጠቀሰው 14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሣ አባ ጽጌ ድንግል ከዚሁ ዘመን ጋርየተያያዘ ድርሰት ደርሷል፡፡ ይህ ድርሰት በግጥም መልክ የተደረሰ በአብዛኛው አምስትስንኞች ያሉት ሲሆን ብዛቱም 15 ያክል ነው፡፡ ይህም ድርሰት «ማኅሌተ ጽጌ» በመባልየሚታወቀው ነው፡፡ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኘው ሁሉ ማኅሌተ ጽጌምእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመሰለ የሚያስረዳ ድርሰት ነው፡፡ እርሷን በአበባ ሲመስልልጇን በፍሬ እርሷን በፍሬ ሲመስል ደግሞ ልጇን በአበባ እየመሰለ ይናገራል፡፡ ነቢዩኢሳይያስ «ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዓርግ ጽጌ እምጉንዱ፤ ከእሴይ ግንድበትር ይወጣል፤ ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል»  /ኢሳ.11÷1/ ብሎ ከእሴይ ዘርየምትገኘውን እመቤታችንን በበትር ከርሷ የሚገኘውን ክርስቶስን ደግሞ በጽጌ መስሎትንቢቱን ተናግሯል፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም ድርሰቱን በዚሁ አንጻር በመቀመር እያንዳንዱንመልክዕ እመቤታችንንና ልጇን አስተባብሮ በጽጌና በፍሬ በመመሰል የእግዚአብሔርንድንቅ ሥራ በምሥጢር በታሪክ፣ በጸሎትና በመሳሰለው መልክ ድንቅ በሆነና በተዋበሁኔታ አዋሕዶ ደርሶታል፡፡
  • ·        የእመቤታችን ስደት እንደ ውሃ ፈሳሽ እንደ እንግዳ ደራሽ አይደለም።  ትንቢት የተነገረለት ነው እንጂ፤ ነቢዩ ኢሳ 19፤1 “እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይወርዳል” በማለት ተናግሯል።  በዚህም ግብጽ በስደት ወርዶ ሃገሪቱን መባረኩንና፤ ጣዖታትን መሰባበሩን ሲያጠይቅ ነው።  በዚህ ስደት እመቤታችን ብዙ ችግርና ኃዘን ተፈራርቀውባታል።  የሌሊቱ ቁር የመዓልቱ ሐሩር የአሸዋው ግለት ጽጌረዳ የመሰለ መልኳን አጠውልጎባታል።  ይህንን አባ ጽጌ ማርያም በማህሌተ ጽጌ ድርሰታቸው “ የሮማ ሽቱ የምትሆኚ ማርያም ሆይ በረሃብ፤ አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በልቅሶ እና በስደት የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እህትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህም ፍጻሜ የሌላውን ደስታሽን እካፈል ነበር” ብሏል
  • ·        በወርኃ ጽጌ የሚታሰበው የ እመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስደት ነው።  የጌታን መወለድ በተስፋ ይጠባበቁ የነበሩ”ሰብዓ ሰገል” መወለዱን የሚያበስር ኮከብ “ በምስራቅ አይተው ሊሰግዱለት ወደ ቤተልሔም መጡ። በዚያም የተወለደው የአይሁድ ጌታ የት ነው? እያሉ ጠየቁ።  ይህ ዜና በንጉስ ሄሮድስ ይህንን ያስብ እንጂ ሁሉን የሚያውቅ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ በቅዱስ ዮሴፍ ወደ ግብጽ እንዲሰደዱ ነገረው።  በዚህም የተነሣ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በምድረ ግብጽ በርሃ ለበርሃ ተንከራተዋል።
  • ·        ይህን ወር የ እመቤታችንን ስደት አስበን በደረሰባት መከራ አዝነን የምናሳልፈው ብቻ አይደለም የራሳችንን ሕይወት የምንቃኝበት የጎበጠውንና የጎደለውን ምግባራችንን ለማቅናት የምንነቃቃበት እንጂ “አምላኬ ተሰዶ ከወጣሁበት ገነት ባይመልሰኝ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነበርኩ” በማለት የምናለቅስበት ጭምር መሆን አለበት።  ሄሮድስ እመቤታችንን ከምድረ ገሊላ ከ እነ ልጇ እንዳሰደዳት ዛሬም በኑፋቄና በትዕቢት በክፋት ተይዘው ከሕይወታቸው እና ከልቦናቸው አውጥተው የሚያሳድዷትም ሁሉ አጥብቀው ራሳቸውን ሊመረምሩ ይገባቸዋል።
  • ·        የጻድቁ ተክለ ሐይማኖት ደቀ መዝሙር የነበሩት አባ ገብረ ማርያም በሰቆቃወ ድንግል ድርሰቱ “ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ዘንዶ ከሔሮድስ ልጅሽ በሸሸ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች፤ ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትን በአሸዋ ግለት እንዲቆሳስል ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋይም ያለቅስ ነበር።
  • ·        በየቦታው ምድርን ያስጌጠው አበባ እንዳማረበት እንዲሁ አይቀርም ይደርቃል ይረግፋል እኩሌታው ግን ረግፎ አይቀርም ፍሬ ያፈራል። እኛም በተሰጠን ጊዜ በ እምነት አንብበን ፍሬ ምግባርን ልናፈራ ይገባል። ችግርን ሐዘንን የምታውቅ በምልጃም እንዳትለየን እንደ አባ ሕርያቆስ “ ድንግል ሆይ ረሃቡን፤ ጥሙን፤ ችግሩንና፤ ሐዘኑን ከእርሱ ጋር የደረሰብሽን ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ” ልንላት ይገባል።

እመቤታችን ለምን ተሰደደች

ትንቢቱን ለመፈጸም
_       ነቢዩ ኢሳይያስ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ግብጽ በፈጣን ደመና ተጭኖ መውረዱን በትንቢት ሲናገር በነቢዩ ሆሴዕም “ልጇን ከግብጽ ጠራሁት” ብሎ ተናግሯል።  ልጇን ከግብጽ ጠራሁት የተባለው ለጊዜው ለያዕቆብ ሲሆን ፍጻሜው ግን ለአምላከ ያዕቆብ ለኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረ ነበር።

በስሙ ለሚነሱ ቅዱሳን ሰማዕታት ስደትን ባርኮ ለመስጠት
ስደትን ለሰው ልጆች ባርኮ የሰጠው ወልደ አብ ክርስቶስ ነው። ክርስቶስ ለመማር፤ለምናኔ፤ ለንስሐ፤ እንዲሁም በሃይማኖት ምክንያት ሃገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ብጹአን ናቸው ማለቱ ነው።

ጣዖት አምልኮን ለማጥፋት
ግብጽ የጣዖት አምልኮ የተስፋፋባት ሃገር ነበረች።  ጣዖት ለማምለካቸውም ብዙ ሕዝብ ተቀስፏል።  ጌታችንም ወደዚያ ቦታ በተሰደደ ጊዜ ጣዖታት ተሰባብረው ጠፍተዋል።

ገዳማተ ግብጽን ለመባረክ
በግብጽ በርካታ የቅድስና ሥፍራዎች አሉ።  እነዚህም ደብረ ቁስቋም፤ ደብረ ምጥማቅ፤ ገዳመ አስቄጥስን፤ ደብረ አባ መቃርስ በመባል የሚታወቁ ሥፍራዎችን ለመባረክ ወደ ግብጽ ተሰደደ።

በተጨማሪ ለማንበብ በዚህ ድረ ገጽ ይጎብኙ

No comments:

Post a Comment

ደ/ም/አ/ቤ/ቅ/ገ/ሰ/ት/ቤት ጎንደር